=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ውዱእ እንደ ሽንት ፣ ዓይነ ምድር ፣ በዓይነ ምድር መውጫ በኩል ከሆድ የሚወጣ አየር ፣ ጥልቅ እንቅልፍና የግመል ሥጋ መብላት ያለ ትጥበቱን ግዴታ የሚያደርግ መለስተኛ ክስተት (አል-ሐደሦ አል-አስገር) ሲከሰት የሚፈፀም የግዴታ ጦሃራ (ትጥበት) ነው።.....Read more
የጁምአ ሶላት በጀመአ የሚሰገድ ስግደት ሲሆን በኢማሙ የሚሰጥ ኹጥባ(ስብከት) በውስጡ ይኖረዋል።
የአሏህ መልእክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) ፀሀይ ከወጣችበት ቀን በላጩ ጁምአ ነው። በዚያን ቀን አደም ተፈጥሯል ፤ ጀነትም ገብቷል ፤ ከሷም ወቶባታል» ብለዋል።....Read more
ሶላት ልብን ብርሃን የምታድርግ ፣ የስኬት ሚስጥር ፣ የጀነት ቁልፍና ከአሏህ ጋር ያለንን ትስስር የምናጠነክርበት ፣ የአሏህን ውዴታ የምናገኝበት ፣ ለአሏህ ትእዛዝ ያለንን ታዛዥነት ፣ ባርነታችንንና ለማኝነታችነን የምንገልፅባት ብቸኛዋ የኢባዳ ተግባር ናት። ሶላት በጭንቀት ጊዜ እረፍትን ሰጭ ፣ ለችግሮች መፍትሄና የሃጥያቶች ማበሻ ናት።....Read more
ፍርሃት ሲያካብብህ ሀዘን ሲያንዣብብህ እና ትካዜ ሊያስርህ ሲሻ ወዲያውኑ ወደ ሶላት ተነሳ ነፍስህ ትረጋጋለች ፤ ውስጥህም ሰላም ያገኛል። ሶላት በአሏህ ፈቃድ የሀዘንና የጭንቀት ባህርን የመቅዘፍ እንዲሁም ትካዜን የማባረር ኃይል አላት። ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) አንድ ጉዳይ ሲያስጨንቃቸው «ቢላል ሆይ በሶላት አሳርፈን» ይሉ ነበር።....Read more
ዱአ አሏህን ለዚህም ሆነ ለመጭው አለም እርዳታን የምንጠይቅበት ታላቅ መንፈሳዊ ኢባዳ ነው። በቃንቇ ደረጃ ዱአ ማለት የእርዳታ ጥሪ ማድረግ ወይም መለመን ፣ መጠየቅ ፣ እርዳታን መሻት ማለት ነው። በሸሪአ ፍች መሠረት ደግሞ ዱአ ማለት አሏህ(ሱ.ወ.ተ) የሆነ ነገር እንዲሰጠን እንዲያጐናፅፈን እና ከመቅሰፍት ፣ ከመከራከና ከችግር እንዲጠብቀን አሏህን መለመን ነው።....Read more
ሶላት ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት ሲሆን ከአሏህ(ሱ.ወ.ተ) ጋር ያለንን ትስስር ወይም ግንኙንነት የምናጠነክርበት ፣ ለኒዕማዎቹ ሁሉ የምናመሰግንበትና ልቅናውን የምናወሳበት ቢሆንም ብዙ ብዙዎቻችን ግን አንሰግድም። ልክ አካላችን ምግብና ውሃ እንደሚያስፈልገው ሁሉ ነፍሳችነም መንፈሳዊ የሆኑ ነገሮች ያስፈልጓታልና ራሳችነን በአምልኮት ተግባራት ልናንፅ ይገባል። ከነዚህ የአምልኮት ተግባራት መካከል አንደኛውና ወሳኙ የሆነው ደግሞ ሶላት ነው።
ረሱል(ሰ.ዐ.ወ): አሏህን የሚያወሳና የሚያወሳ ሰው ንፅፅሩ ልክ ህያው እንደሆነ(በህይወት እንዳለ ሰው)ና በሙት ይመሰላል(ልክ እንደሞተ ሰው ነው) ብለዋል።....Read More
ዱዓ ላይ ያለን ግንዛቤ ምን ያህል ነው?
አኽዋን ወል አኸዋት(ወንድም ና እህቶቼ) ዱዓ ላይ ያለን ግንዛቤ ምን ያህል ነው?
ዱዓ ላይ መበረታት ያስፈልጋል። ከአላህ እርዳታ እምንተይቅበት ብቸኛው መንገድም ነዉ። ቃለ ረሱል (ሰ.ዐ.ወ ) የሰማይን በር ያንኳኳ ሳይከፈትለት አይቀርም ብለዋል። አዎ በመተናነስ ፣ ለሊት ላይ በመቆም ያ– አላህ ያ— ወዱድ ያ— ሙጂብ ብለን በሚወዳቸው 99 ስሞቹ እየተጣራን አልቅሰን በረቹን ስናንኳኳ አላህ የረህመት በሩን ይከፈፍትልናል።....Read more![]()
![]()
![]()
![]()
![]()
![]()
![]()
![]()
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|